156
ኢ.ኤም.ዋይ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር
ለባለአክሲዮኖች በሙሉ
ኢ.ኤም.ዋይ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀጽ 393 እና 394 እንዲሁም በአክሲዮን ማሕበሩ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 10 የባለ አክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ዕሁድ ሕዳር 19 ቀን 2016 ከጧቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ፒያሳ በሚገኘው በሀይከን ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል።
ስለሆነም በስብሰባው ላይ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት እንድትገኙ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል።
የዕለቱ ስብሰባ አጀንዳዎች፡
- የአክሲዮን ማሕበሩን የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የኦዲት ሪፖርት ማድመጥና ማፅደቅ
- የውጭ ኦዲተሩን መሰየምና ማፅደቅ
- አዳዲስ አባላትን በመቀበል የማሕበሩን ካፒታል ስለማሳደግ መወያየት እና ማጽደቅ
- በተጓደለ ቦርድ አባል ምትክ አዲስ አባል መሾምና ማፅደቅ
ማሳሰቢያ፦
በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባዔው ከመካሔዱ በፊት ቤተል ፋሚሊ ታወር 312 በሚገኘው የአክሲዮን ማሕበሩ ቢሮ በአካል በመገኘት የውክልና ቅጽ በመሙላት ውክልና መስጠት የምትችሉ ሲሆን ተወካዮቻችሁ በሰነዶች ማረጋገጫ መ/ቤት የተረጋገጠ የውክልና ፎርሙን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን እንዲሁም የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዘው እንዲቀርቡ በማድረግ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።
የዳይሬክተሮች ቦርድ
ኢ.ኤም.ዋይ ትሬዲንግ አ/ማ