76
ኢ.ኤም.ዋይ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር
ለባለአክሲዮኖች በሙሉ
ኢ.ኤም.ዋይ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀጽ 393 እና 394 እንዲሁም በአክሲዮን ማሕበሩ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 10 የባለ አክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ እና 2ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ዕሁድ ጥር 04 ቀን 2017 ከጧቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ መካኒሳ ሳርቤት በሚገኘው ቢላሉል ሀበሺ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል።
ስለሆነም በስብሰባው ላይ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት እንድትገኙ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል።
የዕለቱ ስብሰባ አጀንዳዎች፡
- የአክሲዮን ማሕበሩን የ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና ሪፖርት ማድመጥና ማፅደቅ
- የውጭ ኦዲተሩን መሰየምና ማፅደቅ
- አዳዲስ አባላትን በመቀበል የማሕበሩን ካፒታል ስለማሳደግ መወያየት እና ማጽደቅ
- በተጓደለ ቦርድ አባል ምትክ አዲስ አባል መሾምና ማፅደቅ
ማሳሰቢያ፦
በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባዔው ከመካሔዱ በፊት ቤተል ፋሚሊ ታወር 312 በሚገኘው የአክሲዮን ማሕበሩ ቢሮ በአካል በመገኘት የውክልና ቅጽ በመሙላት ውክልና መስጠት የምትችሉ ሲሆን ተወካዮቻችሁ በሰነዶች ማረጋገጫ መ/ቤት የተረጋገጠ የውክልና ፎርሙን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን እንዲሁም የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዘው እንዲቀርቡ በማድረግ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።
የዳይሬክተሮች ቦርድ
ኢ.ኤም.ዋይ ትሬዲንግ አ/ማ